Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 107:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የምስጋና መሥዋዕትንም ይሠውለት፥ በእልልታም ሥራውን ይንገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የምስጋናም መሥዋዕት ያቅርቡለት፤ ሥራውንም ደስ በሚል ዝማሬ ይግለጹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡለት፤ በደስታ መዝሙርም ሥራውን ይግለጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 107:22
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፥


አልሞትም፥ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የጌታንም ሥራ እናገራለሁ።


ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና።


እንግዲህ ዘወትር ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት አድርገን በእርሱ በኩል እናቅርብለት።


ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥ የጌታንም ስም እጠራለሁ።


ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥ መጠለያዬም ጌታ ነው ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።


የሚያቀርውም ለምስጋና ቢሆን፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ እርሾ ያልነካው በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “ጌታን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።


ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለጌታ ምንን እመልሳለሁ?


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፥ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል።


እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፥ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለጌታ እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች