18 ሰውነታቸው መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
18 ሰውነታቸው የምግብ ዐይነት ሁሉ ተጸየፈች፤ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
18 ምግብ ስላስጠላቸው፥ ለመሞት ተቃርበው ነበር።
ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፥
ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።
እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ እኩሌታ ከሕይወት ልለይ ይገባልን? በቀረው ዘመኔስ ወደ ሲኦል በሮች መግባት አለብኝን? አልኩ።
የሞት በሮች ተገልጠውልሃልን? የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን?