Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 105:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ! ጌታን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ድንቅ ሥራውን አውሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አሳውቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ ያደረገውንም ሁሉ ለአሕዛብ ንገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 105:1
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ።


ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም ትእዛዝ በታች ነበሩ።


አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ! እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።


ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።


ሃሌ ሉያ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ።


የይዝራኤላዊው የኤታን ትምህርት።


ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ፥


ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው፥ ጌታን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።


በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤ “ጌታን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።


ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅከው፥ የዳኑትም እንዲሻገሩ ጥልቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?


እንዲህም ይሆናል፥ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ ጌታም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚተርፉ ይኖራሉ። ደግሞም ጌታ የጠራቸው ይገኛሉ።


በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል እንዲህ ይባላል፦ ‘እግዚአብሔር ምን አደረገ!’


በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው፤” አለ።


“የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”


በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች