Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 103:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታ ርኅሩኅና ቸር ነው፥ ከቁጣ የራቀ ፍቅሩም የበዛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ፣ ለቍጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው። በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወደ ተራ​ሮች ይወ​ጣሉ፥ ወደ ሜዳ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ህ​ላ​ቸው ስፍ​ራም ይወ​ር​ዳሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 103:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለመስማትም እንቢ አሉ፥ በመካከላቸው ያደረግኸውን ተአምራት አላስታወሱም፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፥ በዓመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ፤ አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፥ ቸር፥ ርኅሩኅ፥ ለቁጣ የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ፥ አልተውካቸውምም።”


ከጌታ ጋር ጽኑ ፍቅር፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና እስራኤል በጌታ ይታመን።


ጌታ ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቁጣ የራቀ፥ ጽኑ ፍቅሩም ብዙ ነው፥


በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደምን በዛች!


አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥


አቤቱ፥ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህና፥ ጽኑ ፍቅርህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።


ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ ጌታም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፤ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።


ለብዙ ሺህ ትውልድ ጽኑ ፍቅርን ታሳያለህ፥ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ፤ ታላቅና ኃያል አምላክ ሆይ! ስምህ የሠራዊት ጌታ ነው።


ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ ጌታ አምላካችሁም ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።


ወደ ጌታ ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አስቀድሜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የፈለግሁትም ለዚህ ነበር፥ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉ የምትመለስ አምላክ እንደሆንህ አውቄ ነበርና።


ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።


‘ጌታ ታጋሽና ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ በደልንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን በደል እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።’


ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን አደርጋለሁ።


በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች