Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 102:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በመንገዴ ጉልበቴ ዛለ፦ ዘመኔም አጠረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እኔም እንዲህ አልሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፤ ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “አምላክ ሆይ! የአንተ ዘመን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ስለ ሆነ ዕድሜዬን ሳላጠናቅቅ በግማሽ ዕድሜዬ አትውሰደኝ” አልኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 102:24
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ፥ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝና።


ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው።


ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፥ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።


ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ “አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ፤” ይላል።


ከዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውም ጠፋ።


እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።


ዕድሜውንም አሳጠርህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች