Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 102:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፥ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ለዘለዓለም ንጉሥ ነህ፤ ስምህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ገናና ሆኖ ይተላለፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ምሥ​ራቅ ከም​ዕ​ራብ እን​ደ​ሚ​ርቅ፥ እን​ዲሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን ከእኛ አራቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 102:12
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ስምህ ለዘለዓለም ነው፥ ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነው፥


አቤቱ፥ አንተ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።


እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ ‘ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ፤’ ይህ ለዘለዓለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።”


ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘለዓለምም ያው ነው።


ጠላቶች በጦር ለዘለዓለም ጠፉ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረስህ፥ ዝክራቸውም ጠፋ።


የእስራኤል ንጉሥ ጌታ፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ፥ እኔ ፍጻሜም ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።


ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘለዓለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።


መኖሪያህ የዘለዓለም አምላክ ነው፥ የዘለዓለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፥ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።


እኛ የትናንት ብቻ ነን፥ ምንም አናውቅም፤ ቀኖቻችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ናቸውና።


እንደ አበባ ይፈካል፥ ይረግፋልም፥ እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።


ማልዶ ያብባል፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።


እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም እረገፍሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች