Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እኔ ጥበብ፥ በብልሃት ተቀምጫለሁ፥ እውቀትንም ጥንቃቄንም አግኝቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እኔ ጥበብ ከማስተዋል ጋራ አብሬ እኖራለሁ፤ ዕውቀትና ልባምነት ገንዘቦቼ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እኔ ጥበብ፥ ማስተዋል አለኝ፤ ዕውቀትና ትክክለኛ አስተያየት የእኔ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እኔ ጥበብ ምክርን አሳደርሁ፥ ዕውቀትንና ዐሳብንም እኔ ጠራሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 8:12
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሑራም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሞያ ነበር፤ ቀደም ብሎ የሞተው የሑራም አባትም የጢሮስ ተወላጅ ሲሆን እርሱም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሞያ ነበር፤ የሑራም እናት የንፍታሌም ነገድ ተወላጅ ነበረች፤ ሑራም በእጅ ጥበብ ብዙ ልምድ ያለው ብልህ ሰው ነበር፤ ከንጉሥ ሰሎሞን በተደረገለት ጥሪ መሠረት መጥቶ የተመደበለትን የነሐስ ሥራ ሁሉ ሠራ።


ደግሞም ለጌታ ቤት አደባባዮችና በዙሪያው ለሚሆኑ ጓዳዎች፥ ለእግዚአብሔርም ቤት ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት፥ ለንዋየ ቅድሳቱም ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ያሰበውን ንድፈ ሐሳብ ሁሉ ሰጠው።


ዳዊትም፦ “የሥራውን ሁሉ ንድፈ ሐሳብ እንዳውቅ ይህ ሁሉ በጌታ እጅ ተጽፎ መጣልኝ” አለ።


ይሁዳም ወደ ኋላው በተመለከተ ጊዜ፥ እነሆ፥ ጦርነቱ በፊቱና በኋላው ነበረ፤ ወደ ጌታም ጮኹ፥ ካህናቱም መለከቱን ነፉ።


አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፥ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።


ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ተመልከቱ፥ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሑር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው።


ብልሃትን ለአላዋቂዎች ለመስጠት ለወጣቶችም እውቀትንና ጥንቃቄን፥


እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥ እናንተም ሞኞች አስተውሉ።


ይህንም ብልሃት አምላኩ ያሳውቀዋል ያስተምረውማል።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው።


እንደ ፈቃዱና እንደ ምክሩ ሁሉን የሚያከናውን እንደ እርሱ ዓላማ የተወሰንን በክርስቶስ በርስትነት ተቀበልን።


ጸጋውንም አበዛልን። በጥበብና በአእምሮ ሁሉ፥


በዚህም ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት እንድትታወቅ ነው።


የጥበብና የእውቀት ሀብት ሁሉ ተሰውሮ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነውና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች