Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 6:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ከሌላይቱም ሴት አታላይ ምላስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሷም ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ ልዝብ አንደበት ካላት ባዕድ ሴት ትጠብቅሃለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከመጥፎ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ይረዱሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ከጐልማሳ ሚስት፥ ከሌላዪቱም አንደበት ነገረ ሠሪነት ትጠብቅህ ዘንድ ትእዛዜን ጠብቅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 6:24
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእንግዳይቱ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከማትታወቀው ሴት፥


ከአምንዝራ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥ ቃሏን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት።


ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ አፍዋም ከዘይት የለዘበ ነውና፥


እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።


እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፥ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።


ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ? የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ?


በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፥ በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች