Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሁለንተናህ ተበልቶ ከማለቁ የተነሣ በሞት ጣዕር ተይዘሃል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሰውነትህ በደከመ ጊዜ፥ ኋላ ትጸጸታለህ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 5:11
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና።


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


ውኃውንም እንድትጠጣ ካደረጋት በኋላ እንዲህ ትሆናለች፤ የረከሰች ብትሆንና ለባልዋ ፍጹም ታማኝ ባትሆን፥ እርግማንን የሚያመጣው ውኃ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያመጣባታል፥ ሆድዋም ይነፋል፥ ጭንዋም ይሰለስላል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?


ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚጣደፍ፥ ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥ ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ።


አስተዋዮች ቢሆኑ፥ ይህንን በተገነዘቡ፥ ፍጻሜያቸውንም ባሰቡ ነበር!


ሌሎች ከኃይልህ እንዳይጠግቡ፥ ድካምህም ወደ ባዕድ ሰው ቤት እንዳይሄድ።


ትላለህም፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ!


ወደ እርሷ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ወደ ሕይወት ጎዳናም አይደርሱም፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች