Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 4:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፥ አሳሳች ቃሎችን ከአንተ አርቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤ ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ክፉ ንግግር ከአፍህ አይውጣ፤ ሐሰትንና ማታለልን ከአንተ አርቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥ ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 4:24
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንደበቱን ሳይገታ፥ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።


የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፥ በውስጣቸውም ምንም ጠማማና ጠመዝማዛ ነገር የለም።


ስለዚህ ርኩሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።


ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።


እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፥ ተንኰልን ሁሉ፥ ግብዝነትን፥ ቅንዓትን ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።


ከንቱና ክፉ ሰው ጠማማ ንግግር ይዞ ይዞራል፥


አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ ጭቅጭቅን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን መምሰል ሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።


አሁን ግን እናንተ ቁጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ፤


የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ፥ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ለምን ትሞታላችሁ?


ጠማማ ልብ ያለው መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል።


ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ።


የጻድቅ ከንፈሮች ደስ የሚያሰኝ ነገርን ያውቃሉ፥ የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነገር ይናገራል።


በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።


አንደበትህን ከክፉ ነገር፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን ከመናገር ከልክል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች