Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 31:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ደም ግባት ሐሰት ነው፥ ውበትም ከንቱ ነው፥ ጌታን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ቍንጅና አታላይ ነው፤ ውበትም ይረግፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን የተመሰገነች ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ቊንጅና ከንቱ ነው፤ ውበትም ይጠፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን ልትመሰገን ይገባታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 31:30
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


በዐሣማ አፍንጫ ላይ የወርቅ ቀለበት፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴት።


ምክንያቱም፥ “ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤


ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።


ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ በጌታ ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ ይመላለሱ ነበር።


ጌታ በሚፈሩት፥ በጽኑ ፍቅሩ በሚታመኑት ይደሰታል።


ውበትዋን በልብህ አትመኘው፥ በዐይኖችዋም አትማረክ።


የአቤሴሎምን ያኽል በመልከ መልካምነቱ የታወቀ ሰው በመላው እስራኤል ከቶ አልነበረም፤ ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ምንም እንከን የሌለበት ሰው ነበር፤


የፀሐይ ቃጠሎ በንዳዱ ሲወጣ ሣሩን ያደርቀዋል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የመልኩም ውበት ይጠፋል፤ እንዲሁ ሀብታም ሰው በመንገዱ ይዝላል።


የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ።


ነገር ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፤ መገረዝም በመንፈስ የሆነ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በፊደል አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።


ነገር ግን በውበትሽ ተመክተሻል፥ በስምሽም አመንዝረሻል ምንዝርናሽንም ከአላፊ አግዳሚው ሁሉ ጋር አበዛሽ።


እግዚአብሔርን የሚፈራ በሁሉም ይዋጣለታልና ይህን ብትይዝ፥ ከዚያም ደግሞ እጅህን ባታርቅ መልካም ነው።


ሃሌ ሉያ። ጌታን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።


ሞገስ ያላት ሴት ክብርን ታገኛለች፥ ኃያላንም ሀብትን ያገኛሉ።።


የትሕትናና ጌታን የመፍራት ውጤት ሀብት፥ ክብርና ሕይወት ናቸው።


“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፥ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።”


ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት፥ ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች