11 የባሏ ልብ ይታመንባታል። መልካም ነገር አይጐድልበትም።
11 ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም።
11 ባልዋ ይተማመንባታል፤ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ አያጣም።
ጐበዝ ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፥ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።
ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ እጅግ ይበልጣል።
ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም።