Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 30:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የጠራ ነው፥ እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ እርሱ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ሁሉ እውነት ነው፤ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 30:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአንተ ግብረ ኃይል አጠቃለሁ፥ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።


ከላይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።


ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥ የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ።


ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።


ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥ ባርያህም ወደደው።


ጌታን፦ “አንተ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ ነህ እለዋለሁ”፥ የምታመንበት አምላኬ ነውና።


ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፥ ትክክለኛና መልካም ነው።


መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፥ ረዳቴና መታመኛዬም፥ ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።


የጌታ ሕግ ፍጹም ነው፥ ነፍስን ይመልሳል፥ የጌታ ምስክር የታመነ ነው፥ የዋሆችን ጠቢባን ያደርጋል።


የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የጌታም ቃል የጠራ ነው፤ ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤


እንዲህም አለ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።


እርሱ ለቅኖች ስምረትን ያከማቻል፥ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፥


የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የጌታም ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።


ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፥ በጌታ የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች