22 አገልጋይ በነገሠ ጊዜ፥ ሞኝ እንጀራ በጠገበ ጊዜ፥
22 ባሪያ ሲነግሥ፣ ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ፣
22 እነርሱም “ባሪያ ሲነግሥ፥ ቦዘኔ ሲጠግብ፥
ለሰነፍ ቅምጥልነት አይገባውም፥ ይልቁንም ባርያ በአለቆች ላይ ይገዛ ዘንድ።
ባርያዎች በፈረስ ላይ ሲቀመጡ መሳፍንትም እንደ ባርያዎች በምድር ላይ ሲሄዱ አየሁ።
ድሆችን የሚያስጨንቅ ድሃ ሰው እህልን እንደሚያጠፋ እንደ ዶፍ ዝናብ ነው።
ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፥ እነሆ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፥ ይጠጡና ይዘፍኑ፥ ይጨፍሩም ነበር።
ጌታዬ፥ ያን ባለጌ ሰው ናባልን ከቁምነገር አይቁጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለሆነ፥ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም አብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጐልማሶች አላየኋቸውም።
የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።
በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥ አራተኛውንም ትሸከም ዘንድ አይቻላትም።
የተጠላች ሴት ባል ባገኘች ጊዜ፥ ሴት አገልጋይም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ።
በማዖን ምድር በቀርሜሎስ ንብረት ያለው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ እርሱም አንድ ሺህ ፍየሎችና በቀርሜሎስ የሚሸልታቸው ሦስት ሺህ በጎች ነበሩት።