Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 30:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነርሱም ሲኦልና የማትወልድ ማኅፀን፥ ውኃ የማትጠግብ ምድርና፦ “በቃኝ” የማትል እሳት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነርሱም መቃብር፣ መካን ማሕፀን፣ ውሃ ጠጥታ የማትረካ ምድር፣ ‘በቃኝ’ የማይል እሳት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነርሱም፦ “መቃብር፥ መኻን ሴት፥ ዝናብ የሚያስፈልገው ደረቅ ምድርና ከቊጥጥር ውጪ የሆነ የእሳት ቃጠሎ” ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 30:16
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሲኦልና ጥፋት እንደማይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዐይን አይጠግብም።


በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።


ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት፥ ያዕቆብንም፦ ልጆች ስጠኝ፥ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው።


አልቅት “ስጠን ስጠን” የሚሉ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉት። ሦስቱ የማይጠግቡ አራቱም፦ “በቃን” የማይሉ ናቸው፥


ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፤ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤ መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋር ወደዚያ ይወርዳሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች