Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 28:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ስግብግብ ሰው ክርክርን ያነሣሣል፥ በጌታ የሚታመን ግን ይጠግባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሥሥታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ግን ይበለጽጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 28:25
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ከሃይማኖት ጋር ያለኝ ይበቃኛል ማለት ትልቅ ጥቅም የሚያስገኘ ነው፤


በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥ ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል።


በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፥ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።


የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።


ጥላቻ ክርክርን ታስነሣለች፥ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ትከድናለች።


ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል፥ በጌታ የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል።


ቁጡ ሰው ክርክርን ያነሣሣል። ወፈፍተኛ ሰውም ኃጢአትን ያበዛል።


ፌዘኛን ብታስወጣ ክርክር ይቆማል፥ ጠብና ስድብም ያልቃል።


ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥ እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል።


የዐይን ብርሃን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ወሬም አጥንትን ያለመልማል።


ቁጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፥ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል።


ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።


ጌታም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።


ጌታ የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፥ የክፉዎችን ምኞት ግን ይገለብጣል።


ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፥ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች