5 ግልጽ ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
5 የተገለጠ ዘለፋ፣ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።
5 በግልጽ የሚነገር ተግሣጽ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል።
በምላሱ ከሚሸነግል ይልቅ ሰውን የሚገሥጽ በኋላ ሞገስ ያገኛል።
ሌሎቹ ደግሞ እንዲፈሩ፥ ኃጢአት የሚሠሩትን በሁሉ ፊት ገሥጽ።
ነገር ግን እነርሱ ከወንጌሉ እውነት ጋር በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ፥ በሁሉም ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፦ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እንደ አይሁድ ሳይሆን እንደ አሕዛብ የምትኖር ከሆነ፥ አሕዛብ አይሁድ እንዲሆኑ ለምን ታስገድዳቸዋለህ?”
“ወንድምህ ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ገሥጸው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ታተርፈዋለህ፤
“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።