20 ሲኦልና ጥፋት እንደማይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዐይን አይጠግብም።
20 ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣ የሰውም ዐይን አይረካም።
20 ሞትና መቃብር በቃን እንደማይሉ፥ የሰው ምኞትም እንደዚሁ ነው።
ነገር ሁሉ ያደክማል፥ ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም፥ ዐይን ከማየት አይጠግብም፥ ጆሮም ከመስማት አይሞላም።
ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፥ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን ምኞት፥ በኑሮ ደረጃ መመካት፥ ከዓለም ነው እንጂ ከአብ አይደለም።
የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም።
በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።
አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።
ዓይንህና ልብህ ግን ለተጭበረበረ ትርፍ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”
ቀና ብለህ እያየኸው ይጠፋል፥ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።
ሲኦልና ጥፋት በጌታ ፊት የታወቁ ናቸው፥ ይልቁንም የሰዎች ልብ የታወቀ ነው።
ሲኦል በፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ለጥፋትም መጋረጃ የለውም።
ውኃ ፊትን እንደሚያሳይ፥ እንዲሁ የሰው ልብ ለሰው ይታያል።
እናንተ ብዙ ነገርን ፈልጋችሁ፥ እነሆ ጥቂት ሆነ፤ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። በምን ምክንያት? ይላል የሠራዊት ጌታ። ምክንያቱም እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ስለፈረሰ ነው።
ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፤ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤ መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋር ወደዚያ ይወርዳሉ።