15 በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፥
15 ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት፤
15 ተጨቃጫቂ ሚስት እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት፤
ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ኀዘን ነው፥ ጠበኛም ሚስት ሳያቋርጥ እንደሚያንጠባጥብ ውሃ ናት።
ከጠበኛና ከቁጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ በውጪ በቤት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ከመቀመጥ በሰገነት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።
እርሷንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው።