19 ባልንጀራውን የሚያታልል፦ “ስቀልድ ነው” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።
19 “ቀልዴን እኮ ነው” እያለ ባልንጀራውን የሚያታልል ሰውም እንደዚሁ ነው።
የሚያጸይፍ ነገር፥ ተራና የእንዝህላል ንግግርም ፈጽመው በመካከላችሁ አይኑሩ፤ ይልቁን አመስጋኞች ሁኑ።
ክፉ ነገር ማድረግ ለአላዋቂ ጨዋታ ነው፥ እንዲሁም ጥበብ ለአስተዋይ ነው።
ልብ ለሌለው ሰው ስንፍና ደስታ ናት፥ አስተዋይ ግን አካሄዱን ያቀናል።
ሰነፉ በኃጢአት ያፌዛል፥ በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች።
የበደላቸውን ዋጋም ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤
በባልንጀራህ ላይ በከንቱ ምስክር አትሁን፥ በከንፈርህም አታባብለው።