16 በጣም እንዳትጠግብና እንዳትተፋው፥ ማር ባገኘህ ጊዜ የሚበቃህን ብላ።
16 ማር ስታገኝ በልክ ብላ፤ ከበዛ ያስመልስሃል።
16 ሲበዛ እንዳያስጠላህ ከሚያስፈልግህ በላይ ብዙ ማር. አትብላ፤
ብዙ ማር መብላት መልካም አይደለም፥ ክቡር ነገሮችን መፈለግ ግን የሚያስከብር ነው።
መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ ብክነት እንደ ሆነው በወይን ጠጅ አትስከሩ፤
“ነገር ግን ልባችሁ በመጠጥ ብዛትና በስካር፥ ስለ ኑሮም ማሰብ እንዳይዝል፥ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤
ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ።
ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል።
የበላኸውን መብል ትተፋዋለህ፥ ያማረውንም ቃልህን ታጠፋዋለህ።
እንዳይሰለቸውና እንዳይጠላህ፥ አዘውትረህ ወደ ባልንጀራህ ቤት አትሂድ።
እጅግ ጻድቅ አትሁን፥ እጅግ ጠቢብም አትሁን፥ ለምን ራስህን ታጠፋለህ?