Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 24:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በባልንጀራህ ላይ በከንቱ ምስክር አትሁን፥ በከንፈርህም አታባብለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በባልንጀራህ ላይ ያለ ምክንያት አትመስክር፤ በከንፈርህም አትሸንግል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በማንም ሰው ላይ ያለ በቂ ምክንያት አትመስክር፤ በእርሱም ላይ አሳሳች ቃል አትናገር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ልጄ ሆይ፥ ነገሬን ፍራ፥ ተቀበለው፥ ንስሓም ግባ፤ ይህንም በእግዚአብሔር ለሚያምኑ ተናግሬ ፈጸምሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 24:28
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን የሰውነት አካሎች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።


በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር እንደ መዶሻና እንደ ሰይፍ እንደ ተሳለም ቀስት ነው።


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁ አስወግዳችሁታልና እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፤


ነገር ግን በሕጋቸው ‘በከንቱ ጠሉኝ’ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።


እርሱም “ምን ክፉ ነገር ሠራና?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።


ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፥ የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል።


ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር ይጠፋል።


ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር አያመልጥም።


የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።


ለመዘምራን አለቃ የዳዊት ትምህርት።


የሐሰት ምስክሮች ተነሡብኝ፥ የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ።


በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥ ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና።


ጌታም ሰይጣንን፦ “በውኑ አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፥ ያለ ምክንያት ይጠፋ ዘንድ በእርሱ ላይ ብትገፋፋኝም እንኳን፥ እስከ አሁን ፍጹምነቱን ጠብቋል።”


“ሐሰተኛ ወሬ አታሰራጭ፥ ሐሰተኛ ምስክር ለመሆንም ከኃጢአተኛ ጋር አትተባበር።


“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።


“ማናቸውም ሰው ኃጢአትን ቢሠራ፥ በጌታም ላይ ፈጽሞ እምነትን ቢያጎድል፥ በአደራ ከእርሱ ዘንድ የተቀመጠን ነገር ወይም ብድር ወስዶ ባልንጀራውን ቢክድ፥ ወይም ቢቀማ፥ ወይም በባልንጀራው ላይ ግፍ ቢሠራ፥


ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ኃጢአት በአንዱ ቢሠራ፥


“አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም ማንም ሰው ወንድሙን አያታልል።


ባልንጀራውን የሚያታልል፦ “ስቀልድ ነው” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች