Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 24:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ክፉዉን፦ “ጻድቅ ነህ” የሚለውን ወገኖች ይረግሙታል አሕዛብም ይጠሉታል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በደለኛውን፣ “አንተ ንጹሕ ነህ” የሚለውን፣ ሕዝቦች ይረግሙታል፤ መንግሥታትም ያወግዙታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በደለኛውን ንጹሕ የሚያደርግን ዳኛ፥ ሰዎች ይረግሙታል፤ ሕዝቦችም ያወግዙታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ከንጉሥ አንደበት ምንም ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ ከአንደበቱም የሚወጣ ሐሰት የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 24:24
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።


ጉቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፤ ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!


እህልን የሚደብቅ ሰው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፥ በረከት ግን በሚሸጠው ራስ ላይ ነው።


ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፥ በድሆች ላይ ዐይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።


ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤


ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።


ክፉውን መልካም፤ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፤ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፤ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!


እንዳይሰድብህ በደለኛም እንዳትሆን ባርያን በጌታው ፊት በሐሰት አትተች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች