Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፥ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዱና ይጐዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ብልኅ ሰው አደጋ ሲመጣ አይቶ ይሸሸጋል። ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ በመግባት ይጐዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 22:3
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፥ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዱና ይጐዳሉ።


ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፥ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል።


ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ፥ ከወጣቶችም መካከል አንዱ አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


“እናንት አላዋቂዎች፥ እስከ መቼ አላዋቂነት ትወድዳላችሁ? ፌዘኞችም ፌዝን ይፈቅዳሉ? ሞኞችም እውቀትን ይጠላሉ?


የትሕትናና ጌታን የመፍራት ውጤት ሀብት፥ ክብርና ሕይወት ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች