Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 22:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ አስደሳች ነገር ይሆንልሃልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በልብህ ስትጠብቃቸው፣ ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዘወትር ብታስታውሳቸውና ብትጠቀምባቸው ደስ ይሉሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነርሱን በልብህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህ በአንድነት ደስ ያሰኙሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 22:18
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃላትህ ተገኝተዋል እኔም በልቼአቸዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ጌታ ሆይ! በስምህ ተጠርቻለሁና ቃላትህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑኝ።


ጥበብ ወደ ልብህ ትገባለችና፥ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለችና፥


የጠቢባን ከንፈር እውቀትን ትዘራለች፥ የሰነፎች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።


የጻድቅ ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ይመግባሉ፥ አላዋቂዎች ግን ከማስተዋል ጉድለት የተነሣ ይሞታሉ።


ክቡር ነገርን እናገራለሁና ስሙ፥ ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ።


ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፥ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።


እንግዲህ ዘወትር ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት አድርገን በእርሱ በኩል እናቅርብለት።


በእኔ የሚያምን፥ መጽሐፍ እንዳለው፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።”


በአግባብ የተነገረ ቃል፥ በብር ፃሕል ላይ እንደተቀመጠ ወርቅ ነው።


ልቡ ጠቢብ የሆነ አስተዋይ ይባላል፥ በከንፈሩም ጣፋጭ የሆነ ትምህርትን ያበዛል።


በብልሃተኛ ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፥ በትር ግን አእምሮ ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።


መንገድዋ የደስታ መንገድ ነው፥ ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።


ሥርዓትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አወጡ።


ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።


የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።


ከአፍህ የሚወጡትን ፍርዶች ሁሉ በከንፈሮቼ ደገምኳቸው።


ጌታን መፍራት ንጹሕ ነው፥ ለዘለዓለም ይኖራል፥ የጌታ ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ናቸው።


የካህን ከንፈሮች ዕውቀትን መጠበቅ አለባቸው፤ ሰዎችም ሕግን ከአፉ መፈለግ አለባቸው፤ ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ መልእክተኛ ነው።


እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ እነሆ እነርሱን ዛሬ አስታወቅሁህ።


ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሎቼም ጆሮህን አዘንብል።


ከዓይንህ አታርቃቸው፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች