Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 21:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ኀጥእ ፊቱን ያጠነክራል፥ ቅን ሰው ግን መንገዱን ያጸናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ክፉ ሰው በዐጕል ድፍረት ይቀርባል፤ ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ክፉ ሰው “አልተሳሳትኩም” በማለት በግትርነት ይጸናል፤ እውነተኛ ሰው ግን ስለ ራሱ ጠባይ በጥንቃቄ ያስባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ኃጥእ ሰው ያለ ኀፍረት ፊት ለፊት ይቃወማል፤ ቅን ሰው ግን መንገዱን ይረዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 21:29
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፥ ክፉ ግን በክፋቱ ይወድቃል።


አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ መንገዳችንን ይምራ፤


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።


የሠራውን በደል ሁሉ አይቶ ተመልሶአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።


አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።


ሁልጊዜ የሚጠነቀቅ ሰው ብፁዕ ነው፥ ልቡን የሚያጸና ግን በክፉ ላይ ይወድቃል።


ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።


ደንቦችህን ለመጠበቅ መንገዶቼ ምነው በቀኑ።


አሁንም ከዛሬ ጀምራችሁ ወደ ፊት ልብ አድርጉ፥ በጌታ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመቀመጡ በፊት፥


አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።”


ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።


አሁንም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።


ያዘችውም ሳመችውም፥ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦


ጠቢብን የሚመስለው? የነገሮችንስ ትርጒም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱንም ድንዳኔ ትለውጣለች።


ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ።


የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች