Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 21:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፥ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ያሟጥጠዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ ሞኝ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ብልኅ ሰው ብዙ ሀብትና ውድ ነገሮችን በቤቱ ያከማቻል፤ ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ያለውን ሁሉ ያባክናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የተወደደ መዝገብ በጠቢባን አፍ ያርፋል፤ አላዋቂዎች ግን ያጡታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 21:20
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።


እግዚአብሔር በልቡ ደስታን እስካኖረ ድረስ፥ እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግም አያስብም።


ጥበብ ከርስት ጋር መልካም ነው፥ ፀሐይንም ለሚያዩ ሰዎች ትርፍን ይሰጣል።


በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ኃይል አለ፥ የኀጥእ ሰው መዝገብ ግን ሁከት ነው።


የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።


ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “መጋቢ የሚያገለግለው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፤ ‘ይህ ሰው ያለህን ይበትናል፤’ የሚል ክስ በእርሱ ዘንድ አቀረቡ።


ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፤ እርሱም ይጨነቅ ጀመር።


በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬንም እስከ አፉ ሞላህ።


መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።


ሞኞቹ ብልሆቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነውና ከዘይታችሁ ስጡን’ አሉአቸው።


በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።


እንጀራን ለሳቅ የወይን ጠጅንም ለሕይወት ደስታ ያደርጉታል፥ ሁሉም ለገንዘብ ይገዛል።


የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፥ እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም።


የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፥ እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።


ለሚወድዱኝ ርስት አወርሳቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም እሞላ ዘንድ።


የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፥ የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው።


የትሕትናና ጌታን የመፍራት ውጤት ሀብት፥ ክብርና ሕይወት ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች