Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ያርፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከማስተዋል መንገድ የሚርቀውን ሰው ሞት ይጠብቀዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 21:16
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ነፍሴ ወደ ኋላም በሚያፈገፍግ በእርሱ ደስ አትሰኝም።”


ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፅን ከሚሠሩት ጋር ጌታ ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን።


ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በንግግራቸው ይደሰታሉ።


እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።


እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤


ጌታን ከመከተል የተመለሱትን፥ ጌታን ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።


ነገር ግን እርሱ ሙታን ከዚያ እንዳሉ፥ ተጋብዦችዋም በሲኦል ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ አያውቅም።


እነርሱም በጨለማ መንገድ ለመሄድ የቀናውን ጎዳና የሚተዉ፥


በጽድቅ የሚጸና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፥ ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞት ይሄዳል።


ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።


አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፥ በአላዊቅነትም ብዛት ይስታል።


ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች