Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንና መልካም መንገድን ሁሉ ታስተውላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በዚያ ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣ መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ የምልህን ሁሉ ብትሰማ፥ ቀጥተኛ፥ ትክክልና ቅን የሆነውን መንገድ ትገነዘባለህ፤ ልታደርገው የሚገባህንም መልካም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ታውቃለህ፤ መልካም መንገድንም ሁሉ ታቃናለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 2:9
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርሷም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አንሄድባትም’ አሉ።


ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ ጌታ ነኝ።


ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።


ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።


አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥ ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።


በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።


ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።


የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።


እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድም ጎዳና መካከል፥


ክፉዎች ሰዎች ፍትሕን አያስተውሉም፥ ጌታን የሚሹ ግን ሁሉን ያስተውላሉ።


ጌታን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ እርሱን ያስተምረዋል።


በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይታገድም፥ ብትሮጥም አትሰናከልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች