Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ድሀን ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፥ ይልቁንም ወዳጆቹ ከእርሱ ይርቃሉ። እነርሱንም በቃል ቢከተላቸው አንዳች አይረቡትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት! እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ ከቶ አያገኛቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ድኻን የገዛ ወንድሞቹ እንኳ ይጠሉታል፤ ወዳጆቹማ የበለጠ ያርቁታል፤ የቱንም ያኽል ቢጣጣር ወዳጆች አይኖሩትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል፥ የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።


የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።


ድሀ በትሕትና እየለመነ ይናገራል፥ ሀብታም ግን በድፍረት ይመልሳል።


ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኃይሌም ተወችኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ።


እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን?


ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው፥ የሀብታም ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።


ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድ ላይም አጥለቀለቁኝ።


በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።


የሀብታም መዝገቡ የጸናች ከተማ ናት፥ የድሆች ውድቀት ድህነታቸው ነው።


ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ።


ወዳጅህንና የአባትህን ወዳጅ አትተው፥ በመከራህም ቀን ወደ ወንድምህ ቤት አትግባ፥ የቀረበ ወዳጅ ከራቀ ወንድም ይሻላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች