Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፥ የጌታ ምክር ግን እርሱ ይጸናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በሰው ልብ ብዙ ዐሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:21
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፥ ጌታ ግን አካሄዱን ያቀናለታል።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ምሏል፦ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንዳሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።


የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፥ የምላስ መልስ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ “ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ” እላለሁ።


ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።


እንደ ፈቃዱና እንደ ምክሩ ሁሉን የሚያከናውን እንደ እርሱ ዓላማ የተወሰንን በክርስቶስ በርስትነት ተቀበልን።


እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው፥ እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፥ እነርሱ ግን ብዙ ብልሃትን ፈለጉ።


ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።


ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።


እናንተ ክፋ ነገርን አሰባችሁብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው።


መልካም ሰው ከጌታ ዘንድ ሞገስን ያገኛል፥ ተንኰለኛውን ሰው ግን ጌታ ይፈርድበታል።


አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።


የሰው ቸርነት የእርሱ ፍሬ ነው፥ ከሐሰተኛ ሀብታምም እውነተኛ ድሀ ይሻላል።


ቃሎቼም በእናንተ ላይ ለክፋት በእርግጥ እንደሚጸኑ እንድታውቁ በዚህች ስፍራ እቀጣችኋለሁ፤ ይህም ለእናንተ ምልክት ይሆናል፥ ይላል ጌታ።


አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።


ለእናንተም፦ እንደ አሕዛብና እንደ ምድር ወገኖች እንሆናለን፥ እንጨትና ድንጋይም እናመልካለን የሚል ከልባችሁ የወጣ አሳብ አይፈጸምላችሁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች