Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዕውቀት አልባ የሆነ ቀናኢነት መልካም አይደለም፤ ጥድፊያም መንገድን ያስታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዕውቀት ያልተጨመረበት ትጋት ጠቃሚ አይደለም፤ በችኰላ የሚሮጥ ሰው መንገዱን ይስታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ነፍስ ዕውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:2
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል፥ ችኩል ሰው ግን ለመጉደል ይቸኩላል።


ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ እጸልያለሁ፤


በችኮላ የሚናገረውን ሰው አየኸውን? ከእርሱ ይልቅ ለሰነፍ ተስፋ አለው።


ለእግዚአብሔር ቅንዓት እንዳላቸው እመሰክርላቸዋለሁ ነገር ግን ቅንአታቸው በእውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም።


ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።


ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ “የሚያምን አያፍርም።”


የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፥ ሀብታም ለመሆን የሚቸኩል ግን ሳይቀጣ አይቀርም።


ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ እውቀትን አስተማረ፥ እርሱም ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና ፈላለገ አስማማም።


በነፍስህ ለቁጣ ችኩል አትሁን፥ ቁጣ በአላዋቂ ብብት ያርፋልና።


ምቀኛ ሰው ሀብታም ለመሆን ይጣደፋል ችጋርም እንደሚመጣበት አያውቅም።


ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት ለሙግት ወደ ሽንጎ ፈጥነህ አትውጣ፥


ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።


የጻድቅ ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ይመግባሉ፥ አላዋቂዎች ግን ከማስተዋል ጉድለት የተነሣ ይሞታሉ።


ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።


“በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ይወቅ። በሐሰት ሄጄ እንደሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኩላ እንደሆነ፥


ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች