Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 18:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለሀብታም ሰው ሀብቱ እንደ ጸናች ከተማ ናት፥ በአሳቡም እንደ ረጅም ቅጥር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ እንደማይወጣ ረዥም ግንብም ይቈጥሩታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሀብታሞች ግን ሀብታቸው በከተማ ዙሪያ እንዳለ ከፍተኛና ጠንካራ ግንብ የሚጠብቃቸው ይመስላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥ ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 18:11
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሀብታም መዝገቡ የጸናች ከተማ ናት፥ የድሆች ውድቀት ድህነታቸው ነው።


የጥበብ ጥላ እንደ ገንዘብ ጥላ ናትና፥ የእውቀትም ብልጫዋ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን መስጠትዋ ነው።


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።


በቁጣ ቀን ሀብት አትረባም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


ሀብታም ሰው ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል፥ አስተዋይ ድሀ ግን ይመረምረዋል።


ተናገር፥ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰውም ሬሳ እንደ ጉድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች