Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 16:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ ስሜቱን የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጕልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ኀይለኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል፤ ብዙ ከተሞችን በጦርነት ድል ነሥቶ ከመያዝ ይልቅ ራስን መቈጣጠር ይበልጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 16:32
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የውሃ የውሃማ በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋር አይሻሉምን? እንዲህ ከሆነማ በእነርሱ ታጥቤ በነጻሑ ነበር!”


ጌታ ርኅሩኅና ቸር ነው፥ ከቁጣ የራቀ ፍቅሩም የበዛ።


ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።


ቁጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፥ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል።


ከዕቡያን ጋር ምርኮ ከመካፈል ከትሑታን ጋር በተዋረደ መንፈስ መሆን ይሻላል።


የሸበተ ጠጉር የክብር ዘውድ ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል።


ዕጣ በጉያ ይጣላል፥ መደብዋ ሁሉ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።


በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥ ገር ምላስ አጥንትን ይሰብራል።


ራሱን መቆጣጠር የማይችል ሰው፥ ቅጥር እንደሌለው እንደ ፈረሰ ከተማ ነው።


የነገር ፍጻሜ ከመጀመሪያው ይሻላል፥ ታጋሽም ከትዕቢተኛ ይሻላል።


በነፍስህ ለቁጣ ችኩል አትሁን፥ ቁጣ በአላዋቂ ብብት ያርፋልና።


ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።


እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርም የዘገየ፥ ለቁጣም የዘገየ ይሁን፤


እኔም ድል እንደ ነሣሁ፥ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች