Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 16:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እውነተኛ ሚዛንና መመዘኛ የጌታ ናቸው፥ የከረጢት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ሥራ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሐቀኛ መስፈሪያና ሚዛን ከእግዚአብሔር ናቸው፤ በከረጢት ውስጥ ያሉት መመዘኛዎችም ሁሉ ሥራዎቹ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሚዛንና መስፈሪያ ትክክል እንዲሆኑ፥ ለሽያጭ የሚቀርቡት ዕቃዎች ሁሉ ሚዛናቸው የተስተካከለ እንዲሆን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነው፤ ሥራውም የከረጢት ደንጊያ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 16:11
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሐሰት ሚዛን በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፥ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።


ሁለት ዓይነት ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በጌታ ፊት ርኩሳን ናቸው።


ሁለት ዓይነት ሚዛን በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም።


እውነተኛ ሚዛን እውነተኛ የኢፍ መስፈሪያና እውነተኛው የባዶስ መስፈሪያ ይኑራችሁ።


“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥


የክፋት ሚዛንንና የአታላይ መመዘኛ ከረጢት አነጻለሁን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች