Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 16:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የእግዚአብሔር ብይን በንጉሥ አፍ ነው፥ አፉም በፍርድ አይስትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የንጉሥ ከንፈሮች እንደ አምላክ ቃል ይናገራሉ፤ አንደበቱ ፍትሕን ያዛባ ዘንድ አይገባም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንጉሥ የሚፈርደው ከእግዚአብሔር በተቀበለው ሥልጣን ነው፤ ስለዚህ ውሳኔዎቹ ዘወትር ትክክል ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጥበብ በንጉሥ አፍ አለ፥ አፉም በፍርድ አይሳሳትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 16:10
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴፍም፥ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው።


ይህ ጌታዬ የሚጠጣበት፥ የተሰወረ ነገርም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? የፈጸማችሁት ድርጊት ክፉ ነው’” በላቸው።


ፍርድን ወደ እሬት የምትለውጡ፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የምትጥሉ እናንተ ሆይ!


የማይረባውን ቃላት ተናገሩ፤ በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ስለዚህ መርዛም አረም በእርሻ ትልሞች ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት በቀለባቸው።


እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።


በውኑ ፈረሶች በዓለታም መሬት ላይ ይጋልባሉን? ወይስ ሰው በበሬዎች በዚያ ላይ ሊያርስ ይችላልን? ነገር ግን እናንተ ፍርድን ወደ ሐሞት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ እሬት ለወጣችሁ፤


ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።


ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፥ አምላኩንም ጌታን በደለ፤ ወደ ጌታ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ ዐጠነ።


‘እግዚአብሔር ከሰጠን ርስት እኔንም ልጄንም ሊያጠፋን ከተነሣው ሰው እጅ ንጉሡ አገልጋዩን ሊታደግ ይፈቅድ ይሆናል።’


ንጉሥ በፍትሕ አገሩን ያጸናል፥ ጥቅም የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች