Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ጌታን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን መማር ነው፤ ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብን የሚሰጥ ትምህርት ነው፤ ክብርን ለማግኘት በቅድሚያ ትሑት መሆን ያስፈልጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:33
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።


የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፥ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።


የጥበብ መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ የሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋልን ያገኛሉ፥ ውዳሴውም ለዘለዓለም ይኖራል።


ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፥ መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።


የአንበሳ ደቦሎች ተቸገሩ፥ ተራቡም፥ ጌታን የሚፈልጉት ግን መልካሙን ሁሉ አያጡም።


ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”


ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።


ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፥


ተግሣጽን ቸል የሚል የራሱን ነፍስ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚሰማ ግን አእምሮ ያገኛል።


የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፥ የምላስ መልስ ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች