Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጌታ ከኀጥኣን ይርቃል፥ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እግዚአብሔር ከክፉዎች የራቀ ነው፤ ደጋግ ሰዎች ሲጸልዩ ግን ይሰማቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:29
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን።


የኀጥኣን መሥዋዕት በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”


ጌታ ከፍ ያለ ነውና፥ ዝቅተኞችን ይመለከታልና፥ ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ያውቃል።


እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፥ በማመንዘር ከአንተ የሚርቁትን ሁሉ አጠፋኻቸው።


የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋቸዋለሁ።


አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ? በመከራም ጊዜ ለምን ትሰወራለህ?


በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፥


የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።


የዐይን ብርሃን ልብን ደስ ያሰኛል፥ መልካም ወሬም አጥንትን ያለመልማል።


ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል የመለያያ አጥር ሆናለች፤ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች