Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ክፉ መቅሠፍት መንገድን በተወ ሰው ላይ ይመጣል፥ ዘለፋንም የሚጠላ ይሞታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከመንገድ የሚወጣ ሰው ጥብቅ ቅጣት ይጠብቀዋል፤ ዕርምትን የሚጠላ ይሞታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ትክክለኛውን መንገድ ትቶ ስሕተት የሆነ ነገር የሚያደርግ ይቀጣል፤ ተግሣጽንም የሚጠላ ይጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የቅኖች ትምህርት በሚያልፉ ሰዎች ትታወቃለች። ተግሣጽን የሚጠሉ ግን በውርደት ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:10
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም “በእስራኤል ላይ ይህን ከባድ ችግር ያመጣህ አንተ ለካ እዚህ ነህን?” አለው።


ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።


አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምንጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።


የድሀውን ልቅሶ እስኪሰማ ድረስ፥ የችግረኛውን ድምፅ እስኪሰማ ድረስ፥ እርሱን ከመከተል ርቀዋልና፥ ከመንገዱም አንዱንም አልተመለከቱምና።


አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥ ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።


ምክሬን ሁሉ ግን ችላ ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፥


ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ተግሣጼንም ሁሉ ንቀዋልና፥


ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፥ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል።


ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።


ባለ አእምሮ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፥ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።


ሲኦልና ጥፋት በጌታ ፊት የታወቁ ናቸው፥ ይልቁንም የሰዎች ልብ የታወቀ ነው።


የኀጥኣን መንገድ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ እርሱ ግን ጽድቅን የሚከተል ይወድዳል።


መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፥ ደበደቡኝ፥ አላወቅሁምም። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እፈልጋለሁ ትላለህ።


ትላለህም፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ!


በመንገድ በመራሽ ጊዜ ጌታ አምላክሽን በመተው በራስሽ ላይ ይህን አላመጣሽምን?


ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ሰው ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።


ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤


ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ይጠላኛል፤ ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች