Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 11:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፥ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በሀብቱ የሚታመን ሁሉ ይወድቃል፤ ጻድቃን ግን እንደ አረንጓዴ ቅጠል ይለመልማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በሀብታቸው የሚተማመኑ ሰዎች እንደ ቅጠል ይረግፋሉ፤ እውነተኞች ሰዎች ግን እንደ መልካም ተክል ይለመልማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 11:28
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።


በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሮቹን እንደሚዘረጋ፥ ሙቀትም በመጣ ጊዜ እንደማይፈራ፥ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም ከማፍራት እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”


እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።


ነገር ግን የሰው ልጆች ከንቱ ናቸው፥ የሰው ልጆችም ሐሰተኞች ናቸው፥ በሚዛንም ይበድላሉ፥ እነርሱስ በፍጹም ከንቱ ናቸው።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እንድከብር የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘለዓለም ይወርሳሉ።


የሀብታም መዝገቡ የጸናች ከተማ ናት፥ የድሆች ውድቀት ድህነታቸው ነው።


በደል ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?


እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች