Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 11:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለሐሜት የሚሄድ ምሥጢሩን ይገልጣል፥ በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሐሜተኛ ምስጢር አይጠብቅም፤ ታማኝ ሰው ግን ምስጢር ይጠብቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሐሜተኛ ሰው ምሥጢር አይጠብቅም፤ ታማኝ ሰው ግን ምሥጢርን ሰውሮ ይይዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 11:13
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዘዋሪ ሐሜተኛ ምሥጢርን ይገልጣል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ሰውን አትገናኘው።


ሙግትህን ከባልንጀራህ ጋር በቀጥታ ፈጽም፥ የሌላ ሰው ምሥጢር ግን አትግለጥ፥


በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት ወድያና ወዲህ አትመላለስ፤ በባልንጀራህም ሕይወት ላይ መሰነናክል ሆነህ አትቁም፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ከዚህም ጎን ለጎን ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ ፈቶችም ብቻ ሳይሆኑ የማይገባቸውን እየተናገሩ ሰውን የሚያሙና በነገር ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።


ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፦ “ይህን ነገራችንን ለማንም ባትናገሩ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፤ ጌታም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ለአንቺ ቸርነትንና ታማኝነትን እናደርጋለን።”


አለቆቹም ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፥ እርሱም ንጉሡ እንዳዘዘው እነዚህን ሁሉ ቃላት ነገራቸው። ነገሩም አልተሰማም ነበርና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ።


የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።


ይህንን ነገራችንን ግን ብትናገሪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ነጻ እንሆናለን።”


ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።


ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል፥ የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል።


ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።


በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች