Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የጻድቅ ደመወዝ ለሕይወት ነው፥ የክፉ ገቢው ግን ለኃጢአት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የደግ ሰው መልካም ሥራ ሕይወትን ያስገኝለታል፤ የክፉ ሰው ኃጢአት ግን ቅጣትን ያስከትልበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 10:16
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፥ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘለዓለም ሕይወት ነው።


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚማርክ እርሱ ጠቢብ ነው።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አስመሳዮች እያታለሉና እየተታለሉ ከክፋት ወደ ባሰ ክፋት ይሄዳሉ።


ከልብ ክፉ ሐሳብ፥ መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።


ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች