Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ፊልጵስዩስ 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንደ እኔ ሆኖ ስለ ደኅንነታችሁ በቅንነት የሚጨነቅ እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝምና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለ እናንተ ደኅንነት ከልቡ የሚገድደው እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቴዎስ በቀር ሌላ ሰው የለኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከእ​ርሱ በቀር፥ እንደ እኔ ሆኖ በማ​ስ​ተ​ዋል ግዳ​ጃ​ች​ሁን የሚ​ፈ​ጽም የለ​ኝ​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ፊልጵስዩስ 2:20
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአንድ አሳብ ተስማምታችሁና አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ኖሯችሁ ደስታዬን ፈጽሙልኝ።


ነገር ግን ጢሞቴዎስ ልጅ ለአባቱ እንደሚያገለግል ከእኔ ጋር ሆኖ ለወንጌል በማገልገል መፈተኑን ታውቃላችሁ።


ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፥ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና፥ አብሮአችሁ ያለ ሥጋት እንዲቀመጥ አድርጉ።


ይህንንም የተናገረው ለድሆች አዝኖላቸው ሳይሆን ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።


ተቀጣሪ ስለሆነ፥ ለበጎቹም ስለማይገደው ይሸሻል።


ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤


በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስታውሳለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድና በእናትህ በኤውንቄ የነበረ ነው፤ አሁን ደግሞ በአንተ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ።


በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።


ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ከተገረዙትም ወገን የሆኑ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል።


“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፥ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ።”


ጠላትስ ቢሰድበኝ፥ በታገሥሁ ነበር፥ የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ፥ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።


ዳዊት ከሳኦል ጋር የሚያደርገውን ንግግር እንዳበቃ፤ የዮናታን ነፍስ ከዳዊት ነፍስ ጋር ተቆራኘች፤ እንደራሱም አድርጎ ወደደው።


የትዕግሥትና የመጽናናት አምላክ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ መሆንን ይስጣችሁ።


ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳውቅ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃላት እየተመገብክ ያደግህ፥ የክርስቶስ ኢየሱስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።


አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን ዓላማዬንም፥ እምነቴንም፥ ትዕግሥቴንም፥ ፍቅሬንም፥ መጽናቴንም፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች