Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ፊልጵስዩስ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በዚህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም እንዲንበረከኩና

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣ ጕልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህ ለኢየሱስ ስም ክብር፥ በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችም ያሉት ሁሉ በጒልበታቸው ይንበረከካሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይህም በሰ​ማ​ይና በም​ድር በቀ​ላ​ያ​ትና ከም​ድር በታች ያለ ጕል​በት ሁሉ ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይሰ​ግድ ዘንድ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ፊልጵስዩስ 2:10
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም የበኲር ልጁን ወደ ዓለም በላከ ጊዜ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ፤” ይላል።


በዚህም ምክንያት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤


ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ይሰግዳሉ፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው እንዲህ ይላሉ፥


በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል፥ በዘመን ፍጻሜ እንዲሆን እንዳቀደው፥


የእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ አፌዙበት፤


ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን አስረከበ፤ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን አስረከቡ፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ፍርድን ተቀበለ።


ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?


ነገር ግን መለኮታዊ መልስ ምን አለው? “ለበዓል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ።”


ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁም የሰው ልጅ በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቆያል።


በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፥ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፥ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።


ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፥ በፈጠረን በእርሱ በጌታ ፊት እንበርከክ፥


በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች