Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ፊልጵስዩስ 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን በሥጋ መኖር ማለት ለእኔ ፍሬያማ ሥራ የምሠራበት ቢሆን፥ ምን እንደምመርጥ አላውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በሥጋ ከቈየሁ፣ ፍሬያማ ተግባር ይኖረኛል፤ ነገር ግን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይሁን እንጂ በዚሁ ሥጋዊ አካሌ ቀጥዬ የምኖር ብሆን ፍሬ የሚሰጥ ሥራ መሥራት ማለት ነው፤ ሆኖም ግን ቀጥዬ ከመኖርና ከመሞት የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ፊልጵስዩስ 1:22
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት አትኑሩ።


ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።


ነገር ግን ስለ እናንተ በሥጋ መኖሬ ይበልጥ አስፈላጊ ነገር ነው።


“አሁንም፥ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ እንደ አለቆቻችሁ ደግሞ ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቄአለሁ፤


ምንም እንኳ በሥጋ የምንመላለስ ብንሆን፥ ውጊያችንን ግን እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤


እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አቤቱ፥ አትተወኝ።


ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም አይተውት ስለማያውቁት ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል እንደምጋደል እንድታውቁ እወዳለሁና፤


እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝቡን አልጣላቸውም። ወይስ ኤልያስ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እስራኤል እንዴት እንደተከራከረ መጽሐፍ ምን እንደሚል አታውቁምን?


ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፦ “ይህ ከግብጽ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ ተነሥና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን” አሉት።


እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፥ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።


አቢሜሌክም አለ፦ “ይህን ነገር ያደረገውን አላወቅሁም፥ አንተም ደግሞ ምንም አልነገርኸኝም፥ እኔም ከዛሬ በቀር አልሰማሁም።”


ወንድሞች ሆይ! በሌሎቹ ሕዝቦች እንዳገኘሁት በእናንተም ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳቀድሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።


በእነዚህም በሁለቱ አማራጮች መካከል እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች