ዘኍል 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 “ለመገናኛው ድንኳን መገልገያ እንዲሆኑ እነዚህን ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገልግሎታቸው ትሰጣቸዋለህ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 “በመገናኛውም ድንኳን ለአገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ከእነርሱ ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸውም ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን ለሌዋውያኑ ስጣቸው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚከናወነው ተግባር መገልገያ ይሆኑ ዘንድ እነዚህን መባዎች ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸው አገልግሎት በሚያስፈልጋቸው መጠን መድበህ ለሌዋውያን ስጣቸው።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 “ለምስክሩ ድንኳን ሥራ የሚያገለግል ይሆን ዘንድ፥ ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገልግሎታቸው ስጣቸው።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ለመገናኛው ድንኳን ማገልገል ይሆን ዘንድ ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገግሎታቸው ስጣቸው። ምዕራፉን ተመልከት |