Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በባልዋም ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ እርሷም በመርከስዋ ስለ ሚስቱ ቢቀና፤ ወይም እርሷ ሳትረክስ በእርሱ ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና በርግጥም ጐድፋ ብትገኝ ወይም ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና እርሷ ግን ጐድፋ ባትገኝ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ራስዋን ባረከሰች፥ ወይም ራስዋን ሳታረክስ በጥርጣሬ በሚስቱ ላይ የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢመጣ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ምስ​ክ​ርም ባይ​ኖ​ር​ባት፥ በም​ን​ዝ​ርም ባት​ያዝ፥ በባ​ል​ዋም ላይ የቅ​ን​ዐት መን​ፈስ ቢመ​ጣ​በት፥ እር​ስ​ዋም ስት​ረ​ክስ ስለ ሚስቱ ቢቀና ወይም እር​ስዋ ሳት​ረ​ክስ የቅ​ን​ዐቱ መን​ፈስ ቢመ​ጣ​በት፥ ስለ ሚስ​ቱም ቢቀና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በባልዋም ላይ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ እርስዋም ስትረክስ ስለ ሚስቱ ቢቀና፤ ወይም እርስዋ ሳትረክስ የቅንዓት መንፈስ ቢመጣበት፥ ስለ ሚስቱም ቢቀና፤ ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 5:14
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቅንዓት ለሰው የቁጣ ትኩሳት ነውና፥ በበቀልም ቀን አይራራለትምና።


እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።


ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።


ወይም በባልዋ ላይ የቅንዓት መንፈስ መጥቶበት ስለ ሚስቱ በሚቀና ጊዜ ቅንዓትን በሚመለከት ሕጉ ይህ ነው፤ ሴቲቱንም በጌታ ፊት ያቁማት፥ ካህኑም ይህን ሕግ ሁሉ በእርሷ ላይ ይፈጽምባት።


ወይስ ጌታን እናስቀናውን? እኛስ ከእርሱ ይልቅ እንበረታለንን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች