ዘኍል 4:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መግብያ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ የሚገለገሉባቸውንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ እነርሱንም በሚመለከት ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ያድርጋሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 እንዲሁም በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን የአደባባዩን መጋረጃዎች፣ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፣ ገመዶችና ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህም ያገልግሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 እንዲሁም በድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ለሚገኘው አደባባይ የተሠሩትን መጋረጃዎችና አውታሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ በር የሚሆኑትን መጋረጃዎችና ለእነዚህ መገልገያ የተመደቡትን ሌሎችንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ ለእነዚህም ዕቃዎች የሚሆነውን ማንኛውንም አገልግሎት ይፈጽማሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፥ ለማገልገልም የሚሠሩበትን ዕቃ ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህም ያገልግሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን መጋረጃ፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ ለማገልገልም የሚሠሩበትን ዕቃ ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህ ያገልግሉ። ምዕራፉን ተመልከት |