ዘኍል 36:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እነርሱም እንዲህ አሉ፦ “ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርገህ በዕጣ ከፋፍለህ እንድትሰጣቸው ጌታ አንተን ጌታችንን አዘዘህ፤ ጌታም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አንተን ጌታችንን አዘዘ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እንዲህም አሉ፤ “ምድሪቱን በዕጣ ከፋፍለህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ እንድትሰጣቸው እግዚአብሔር አንተን ጌታዬን ባዘዘ ጊዜ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዝዞሃል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “ምድሪቱን በዕጣ ለእስራኤል ሕዝብ እንድታከፋፍል እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዞሃል፤ እንዲሁም የዘመዳችንን የጸሎፍሐድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዞሃል፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጌታችንን አዘዘው፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታችንን አዘዘው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 አሉም፦ ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርገህ በዕጣ ከፍለህ ትሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር አንተን ጌታችንን አዘዘህ፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ትሰጥ ዘንድ አንተን ጌታችንን አዘዘ። ምዕራፉን ተመልከት |