Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 35:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ እንዲሸሽባቸው የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ማናቸውም ሰው፥ በስሕተት ሰውን ቢገድል ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ስድስት ከተሞችን ለሌዋውያን ትሰጣላችሁ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞችን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ስድ​ስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚ​ሸ​ሽ​ባ​ቸው የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ናቸው፤ ከእ​ነ​ዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ ይሸሽባቸው ዘንድ የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 35:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰማሪያዋን፥ ልብናንና መሰማሪያዋን፥


የእስራኤልም ልጆች እንደ ጌታ ትእዛዝ ከርስታቸው እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን ሰጡ።


እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።


ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንና መሰማሪያዋን፥


ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰማሪያዋን፥


ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞት-ዶንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው።


ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።


እነዚህንም ከተሞች ሰጡአቸው፤ በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


እናንተ ደካሞችና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


ከቀኑ ሙቀት ጥላና መከለያ፤ ከውሽንፍርና ከዝናብም መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናል።


ከከተማው ውጭ በምሥራቅ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በደቡብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በምዕራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በሰሜንም በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ትለካላችሁ፥ ከተማውም በመካከል ይሆናል፤ ይህም የከተሞቹ መሰማሪያ ይሆንላቸዋል።


ሳይሸምቅበት፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንገት በእጁ ቢጥለው፥ የሚሸሽበት ስፍራ እኔ አዘጋጅልሃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች